Premise ከሌሎች ጋር ፈር ቀዳጆች ጋር በመሆን Unlock Aidን መስርቷል፡ ይህም ኋላ ቀር የሆነውን የዓለም አቀፍ የልማት ስርዓት ለማሻሻል ይጠቅማል

Pat Tully

በመስከረም ወር አጋማሽ አካባቢ የ Premise ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ሞሪ ብላክማን ከሌሎች 19 የሚሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ለ USAID ዋና ስራ አስኪያጅ ሰማንታ ፓወር ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ የደብዳቤው ዓላማ Unlock Aid የተባለ ድርጅት እንደተመሰረተ ለማሳወቅ ሲሆን ይህም ድርጅት — ከሃያ በሚበልጡ የተለያዩ ድርጅቶች መሪዎች የተመሰረተ ሲሆን ዓላማውም ከራሳችን የፐብሊክ ተቋማት ጀምሮ ስር-ነቀል የሆነ ዓለም አቀፍ ዴቨሎፕመንት እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡ ስራ ፈጣሪዎች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዟቸውን ግብዓቶች ለመግዛት የሚያስችላቸው ለኢንተርናሽናል ልማት ተብሎ ከህዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ኋላ ቀር በሆነ ስርዓት ምክኒያት ገንዘቡን በትክክል ማግኘት አልቻሉም፡፡

Premise እንደ አንድ የዚህ ድርጅት መስራችነቱ፣ ይህን ከሕዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ በዓለም ዙሪያ ለተገቢው ዓላማ እንዲውል ለማድረግ በኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ላይ የሌሉ አዲስ እና ውጤት ተኮር የሆኑ ዘዴዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ “በርካታ የግል ሴክተር ድርጅቶች እና ኢኖቬተሮች እንደ USAID ያሉ እና ሌሎችም ወረርሽኝን፣ የከባቢ ዓየር ለውጥን፣ እንዲሁም ድህነትን ለመዋጋት ትኩረት አድርገው ለሚንቀሳቀሱ የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ኤጀንሲዎች ድጋፍ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡ እነዚህን የተለያዩ ድርጅቶች ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ እንቅፋት የሆኑባቸውን ችግሮች መፍታት፣ ለልማት የሚያስፈልገውን ገንዘብ እና እውቀት በተገቢው መንገድ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ ያስችላል፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ Premise የሚጠበቅበትን አስተዋፆ ለማድረግ ይሰራል፡፡” በማለት የድርጅታችን ስራ አስኪያጅ ብላክማን ተናግረዋል፡፡ እንደ የዓየር ንብረት ለውጥ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመሳሰሉ ትላልቅ ችግሮች ፋታ የማይሰጡ ችግሮች ሲሆኑ፣ ችግሮቹን ለመፍታት እየሰሩ ያሉ የተለያዩ ግዙፍ ድርጅቶችም የሚፈለገውን መፍትሄ በፍጥነት ማቅረብ አልቻሉም፡፡

Premise ችግሮቹን መፍታት የሚያስችል ከዚህ በፊት ያልተሞከረ ዘዴ ይዞ ቀርቧል፡፡ የ Unlocl Aid ድርጅት ዋና ዓላማ እንደ USAID እና የመሳሰሉ ሌሎች የእርዳታ ድርጅቶች በቴክኖሎጂ አማካኝነት ዓለም አቀፍ የልማት ፕሮግራሞቻቸውን ማከናወን እንዲችሉ የሚያስችል ስታንዳርዶችን ማዘጋጀት ነው፡፡

ያነጋግሩን

በጥናቶቻችን ተሳታፊ አባል ከሆኑ፣ እባክዎ የ Premise አካውንት የከፈቱበትን ኢሜል አድራሻ ያስገቡ፡፡

Thankyou for getting in touch